መግቢያ
በኮሬ አፈ ታሪክ መሰረት፣ የኮሬ ሰዎች በ14 ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ከጋሞ ደጋማ አካባቢዎች ተሰድደው እንደመጡ ይነገራል ፡፡ ሌሎች እንደሚሉት ደግሞ ሚስዮናውያን ከመንዝ ወደ አማሮ በ 14ኛው እና በ 15ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ስደተኞቹ ወደ አማሮ በመጡበት ጊዜ የአገሬው ተወላጆች ከመጤዎቹ ጋር ከተዋጉ በኋላ የተወሰኑት ወደ ቡርጂ ፣ ኮንሶ እና ደራሼ ተሰድደዋል ፡፡ ከተወላጆቹ ጋር የተዛመዱ ስደተኞች የሮ መድኀኔ ዓለምን ፣ እቻ ጎርግሶ እና ደርባ መንገሻ ሚካኤል ታቦት ይዘው ሄደው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መስርተዋል። በመጨረሻም በ 14 ኛው ክፍለዘመን መገባደጃ ላይ 23 ቀበሌዎች የያዘ የአማሮ ወረዳ ተቋቋመ ፡፡ እንደዚሁም አሕመድ ግራኝ በ 16 ኛው ክፍለ ዘመን የአማሮ (ኮሬን)ወረዳ ወርሮ አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥሏል ክርስቲያኖችንም አሳድዷል ፡፡
